Tuesday, April 10, 2012

The Monastery of Waldba


ስለዋልድባ ገዳማችን መቅናት ልማትን መቃወም ፣ ምንቀኝነትና  ኋላ ቀርነትም አይደለም ። የመንፈሳዊ እሴታችን የሆነው የዋልድባን ገዳም ህልውና ፤ ጸሎታቸው የሚረዳን መነኮሳት አባቶችቻችን ጽሙና አደጋ  ላይ ስለሚጥለው ነው ።
ለልማት ይገደናል የምትሉ ሆይ ለኢትዮጵያውያን ነገረ እግዚአብሔር ከጉዳዮች በላይ እንደሆነብን እንዴት ዘነጋችሁት?
ልማቱንስ ቤተክርስቲያን( 'ቤተክህነት' አላልኩም) ስትደግፈው አይደል የሚሠምረው?
                                    እንበለ ፈላሲ ኢይባዕ ነጋሲ  




Monday, April 9, 2012

ሰሙነ ሕማማት ሥርዓተ ጸሎት

ከዕለተ ትንሳኤ በፊት ከሆሣዕና እስከ እሁድ ማት፡ እስከ ቅዳሜ ስዑር ማታ ያለው ሰሙን ሰሙነ ሕማማት ይባላል።ይኸውም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለሰው ልጆች የተቀበለው ሕማምና መከራ የሚታሰብብት ነው።በሰሙነ ሕማማት ከሰኞ እስከ አርብ  በቤተክርስቲያን በግልም በማኅበርም የሚደረገው ሥርዓተ ጸሎቱን ፣ምንባባቱን ፣የሚዜመውን፣የስግደቱን ሥርዓት ሁሉ የያዘ ሰነድ እንሆ፡-              
  PDF ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

እግዚአብሔር ሀገራችንና ቤተክርስቲያናችንን ይጠብቅልን።
መልካም የጾም፣የጸሎት፣የሥግደት ጊዜ ያድርግልን።