Thursday, March 22, 2012

የአቡነ ሺኖዳ ኑዛዜ.


by Henok Haile on Thursday, March 22, 2012 at 5:31pm  ·




እኔ አባታችሁና መምህራችሁ ነኝ ፣ ሁላችሁ ልጆቼ ትእዛዜን አዳምጡ በቅድስት ሥላሴ ማመንን እንድትከተሉና እንድትጸኑ እነግራችኋለሁና፡፡
የተወደዳችሁ ልጆቼ እርስ በእርሳችሁ በእውነተኛ ፍቅር ትዋደዱ ዘንድ እለምናችኋለሁ!
የተወደዳችሁ ልጆቼ እለምናችሁዋለሁ በፍጹም ሰብአዊነት መልካምን አድርጉ እለምናችኋለሁ!
የተወደዳችሁ ልጆቼ እለምናችኋለሁ ዓለም እንድታታልላችሁ አትፍቀዱላት እለምናችኋለሁ!
የተወደዳችሁ ልጆቼ እለምናችሁዋለሁ በእግዚአብሔር አገልግሎት ዳተኞችና ቸልተኞች አትሁኑ ብዬ እለምናችኋለሁ!
የተወደዳችሁ ልጆቼ ያለማቋረጥ እና ያለ መታከት እንድትጸልዩ እለምናችኋለሁ!
የተወደዳችሁ ልጆቼ መለያየትን ከሚያመጣ ንግግር አንደበታችሁን እንድትጠብቁ  እለምናችኋለሁ!
የተወደዳችሁ ልጆቼ የተጠመቃችሁባትን ቅድስቲቱን ጥምቀት እንድትጠብቋት  እለምናችኋለሁ!
የተወደዳችሁ ልጆቼ ሰውነታችሁን ለጌታ ንጹሕ አድርጋችሁ እንድትጠብቁ  እለምናችኋለሁ!
የተወደዳችሁ ልጆቼ መብራታችሁ ፈጽሞ እንዲጠፋ አትፍቀዱ ይልቅስ ብርሃንን እንዲሰጥ እንድታደርጉት  እለምናችኋለሁ!
የተወደዳችሁ ልጆቼ እግዚአብሔር የሰጣችሁን ትእዛዝ እንድትጠብቁ  እለምናችኋለሁ!
የተወደዳችሁ ልጆቼ እግዚአብሔርን መፍራት ከእናንተ ጋር እንዲሆን  እለምናችኋለሁ!
የተወደዳችሁ ልጆቼ ልጆቼ እኔ እስከ መቼም አልተኛም … በማንኛችሁም ላይ ቅሬታ የለኝም … ከእግዚአብሔር ትእዛዛት መካከል ለእናንተ አንዲቱንም ከመናገር እንዳልሸሸግሁ እግዚአብሔር ምስክር ነው፡፡ የነገርኳችሁን ሁሉ ከጠበቃችሁ የዕባቡንና የዘንዶውን ራስ ትቀጠቅጣላችሁ፡፡ እናም ያልኋችሁን ካደረጋችሁ የምድርን በረከት ትበላላችሁ፡፡  ያልኳችሁን ካደረጋችሁ ብርሃናዊያን ኪሩቤል ይጠብቋችኋል፡፡ ያልኳችሁን ካደረጋችሁ ሰማያዊ ጸጋ አይጎድልባችሁም፡፡
የተወደዳችሁ ልጆቼ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ፊት ስለ ነፍሴ ጸልዩልኝ ፤  ሳልፈቅዳቸውም ሆነ ካለማወቅ የሠራኋቸውን መተላለፎቼን እንዳይቆጥርብኝ እና  በፊቱ ዕረፍትን ይሰጠኝ ዘንድ ጸልዩልኝ፡፡
ለጳጳሳት ፣ ለማህበረ ካህናት
            ፍቅራችሁንና እየለመንሁ ትፈቱኝ ዘንድ በአክብሮት እማጸናለሁ፡፡ እነሆ አሁን ከእናንተ ርቄ ትቼያችሁ ሔጃለሁ ፣ ፊታችሁንም ለማየት አልችልም፡፡ ሁላችሁም ስለ እኔ በመጸለይ እንድትደክሙ መምህሬ ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲቀበለኝና ይቅር እንዲለኝ በቅዳሴያት ሁሉ እንድታስቡኝ እለምናችኋለሁ፡፡
            የእረኞች ሁሉ እረኛ ክርስቶስ እንደ እርሱ ፈቃድ እና እንደልቡ አሳብ እናንተንና ነገሮቻችሁን ሁሉ የሚመራ ፣ ስለ ነፍሳችሁ መዳን  ጻድቅ እረኛን ይመርጥላችሁ ዘንድ እለምነዋለሁ!!
                                                                                                           ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ

(ይህ የኑዛዜ ቃል በቅዱስነታቸው ቃለ ኑዛዜ ተብሎ በቀብራቸው ዕለት የተነበበ ሲሆን አንዳንዶች ለሁሉም ፓትርያርክ (The Patriarchal Commentary!) የሚነበብ  ነው /Once again as much confusion has arisen this is NOT HH personal will rather it is the Commentary to be read at the funeral of every Patriarch!/  ብለዋል፡፡ ያም ሆነ ይህ ከላይ እንዳያችሁት ተርጉሜዋለሁ!  ትልቅ ምስጋና ቃለ ኑዛዜውን ለላከልኝ ለንፍቀ ዲያቆን ቢሾይ ማርቆስ  (especial gratitude for Sub deacon Bishoy, St Barbara & St Noufer’s Coptic Orthodox Church in Sydney Australia) 

Pope Shenouda III AP

No comments:

Post a Comment